• ንጉሡ ይንገሥ የቀጠላ፡-
    1. ክፉ ሐሳብ መላክ፣
    2. ሁኔታዎችን ማመቻቸት..ነው ፡፡
    እንጂ የማንንም እጅ ይዞ ና ጠምዝዞ ሐጢያት አያሰራም፡፡ ሔዋንንም ቢሆን በቃልና በሐሳብ ነው የማረካት ድርጊቱን ያደረገችው እርስዋ ነች፡፡
    3. ሐሳብን መበላሸት ነዉ
    ለሰው ልጆች ሁሉ ውድቀትና ሰበብ የሆነው የሔዋን ስህተት የመጣው ሰይጣን ሐሳቧዋን አበላሽቶት ነው፡፡ 2ቆሮ.11፤3 ፡፡ ሐሳቡ የተበለሸበት ሰው ወደ ድርጊቱ ለመግባት ቀላል ይሆንለታል፤ ልክ እንደ ቃየን ሁሉ የዳዊት ልጅ አቤሴሎምም ወንድሙን አምኖንን ከመግደሉ በፊት ረጅምና የቆየ የግድያ ሐሳብ አርግዞ ነበር፡፡ ጊዜውና ሁኔታዎች ሲመቻቹለት ደግሞ አስገደለው፡፡ (2ሳሙ.13፤23-29)
    አንዳንድ ጊዜ ክፉ ሐሳብ ያድርና ድርጊቱ ሊቆይ ይችላል፤ ያህን ጊዜ መንቃት ነው፡፡
    ምንም እስካላደረኩ ድረስ ንጹህ ነኝ ማለት አይቻልም፡፡ ቀን በሚጠብቅ ክፉ ምኞት ላይ መንገስ ያስፈልጋል፡፤ እግዚአብሔር ቃኤልን ቀድሞ ያስጠነቀቀው ለዚያ ነበረ፡፡ ደጅህ ላይ ሐጢያት እያደባች ነው ንገስባት አለው፡፡ አለዚያ እርሱዋ ትነግስብሃለች፡፡ ያን ጊዜ ፍቃዱዋን ታደርጋለች፡፡ እግዚአብሄር ወደ ቃየን መጥቶ ከነገረው ነገር የምንማረው ኀጢያት ላይ እኛ መንገስ ካልቻልን ኀጢያት በእኛ ላይ መንገስ ይችላል /ይጀምራል/ ማለት ነዉ፡፡
    /ዘፍ.4፤7/ “ መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን ?መልካም በታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ፈቃድዋም ወደ አንተ ነዉ÷አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት ” አለዉ፡፡
    ያዕቆብ 1፤15 ላይ ሲናገር
    “ ምኞት ጸንሳ ሐጢያትን ትወልዳለች ፡ሐጢያትም ጸንሳ ሞትን ትወልዳለች ”
    ሞት የሚባለው /ውድቀት/ነዉ፤ ከመከሰቱ በፊት ውስጥን ይዞ የሚከርመው ሐሳብ /ምኞት/ ነው፡፡ ምኞት ዝም ከተባለ ቆይቶ ቆይቶ ሀጢያትን ይወልዳል፤ ከዚያም ወደ ሞት ያመጣል፤ይህ ሁሉም ሂደት ነው፡፡ ሐጢያትን፣ሞትንና ውድቀትን በህይወቱ ማየት የማይፈልግ ሰው ራሱን ማንጻት ያለበት ከውስጥ ነው፡፡
    ምን አርግዣለሁ? ብሎ ራስን መጠየቅ፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታን ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ በቅድሚያ ሐሳብ ነው የመጣለት፡፡ “ ዲያቢሎስም ሐሳብ ካስገባ በሆአላ” አስቆሮቶ ይሁዳ ምናልባት ዲያቢሎስ ወደ አዕምሮው የላከበትን ሐሳብ መቃወም ይችል ነበር ፡፡
    ምናልባትም ወደ ሌሎች ደቀመዛሙርትም ዲያቢሎስም ይህንን ሐሳብ አቅርቦም ይሆናል፡፡ ቢሆንም እነርሱ የዲያቢሎስም ሐሳብ ተቃውመውት ይሆናል፡፡ ይሁዳ ግን ሐሳቡን አስተናገደ፤ ወደ ቀጣዩ ና ከባዱ ነገርም አለፈ፡፡
    ሮሜ 6፡12 “...ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ '' ስጋችን ላይ ሐጢያት ሲነግስ እንደ ስጋ ፈቃድ ለመኖር የስጋን ነገር አዘውትረን ለማስብ እንገደዳለን” /ሮሜ.8፡5/

    ውስጡ የተሸነፈዉን ሰው ወደተገዛለት ነገር በቀላሉ መጎተት ይቻላል፡፡ ብዙ የሚያቅተው ከነገሮች ውስጥ መውጣት ሳይሆን ነገሮችን ከውስጥ ማስወጣት ነው፡፡ እስራኤላውያን በእግራቸው ከግብጽ ውስጥ ወጥተው ነበር፡ ነገር ግን በቆይታ እንደታየው ግብጽ በውስጣቸው ነበረ፡፡ ስለዚህም፡-
    /ሥራ.7፡39/ “ለእነርሱም አባቶቻችን ሊታዘዙት አልወደዱም፤ነገር ግን በልባቸው ወደ ግብጽ ተመለሱ ይለናል”፡፡
    ከዓለም ወጥተን ግን ዓለም በውስጣችን ካለ ፡-እየዘመርን፤እየጸለይን፤ ቤተክርስቲያን እየሄድን፤ የሐጢያት ተጠቂዎች ልንሆን እንችላለን፡፡ከግብጽ ወጥተህ ግብጽ ግን ከልብህ ካልወጣ ችግር ነው፡፡
    የሎጥ ሚስት ከሶዶም በእግሩዋ ወጥታለች ነገር ግን ሶዶም ከውስጥዋ አልወጣም ነበርና እንቅፋት ሆነባት፡፡ መቀየር ፣መለወጥ ከውስጥ ነው፡፡
    ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል (በሮሜ 12፡3) “ በአዕምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ......" የሚለን፡፡ ከየ ዕለቱ ኑሮአችን እንኩዋ ብንመለከት አንድ ሰው ወተት ወይም ጎመን የሚጠላ ቢሆን፡ ከፈለገ ቦታ ቢመጣም ወይም ነጻም ቢሆን አይነካውም፡፡
    ሐጢያትን ከውስጥ ስንጠላ አዩኝ አላዩኝ ከሚል መሳቀቅ እንወጣለን፡፡ በዚህም ላይ ውስጣችንን ቦርቡሮ በጊዜ ሒደት ከሚጥለን ነገር እንገላገላለን፡፡ ልክ እንደ ጎመኑ ና ወተቱ የትም ብንሆን ፣መቼም ቢሆን አንነካውም፡፡

    አንድ የእግዚአብሔር ሰው ሲናገር ውስጡ ችግር ያለበት ሰው ያማረ ህንጻ ውስጥ ወይም አውሮፕላን ውስጥ ቢገባ ችግሩ አያቆምም ብሎአል፡፡ የገባበት ቦታ ነገሩን ሊለውጥ ስለማይችል ነዉ፡፡
    ከዚህ በፊት አንድ በጣም ወፍራምና ዕድሜ ጠገብ ዝግባ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በሆነ ወቅት ነፋስ ባልነበረበት ጊዜ በሌሊት ላይ ወድቆ ነዉ የተገኘው፤በዘው ጊዜ የወደቀበት ሁኔታው ሲጠና ዛፉ በከፍተኛ ሁኔታ ውስጡ በብል ተቦርቡሮ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ በቅርፊት ተሸፍኖ ያለ እየመሰለ ኖረ እንጂ፤ነገር ግን ባልታሰበ ቀን ቀን ላይ ነዉ ወድቆ የተገኘዉ፡፡ ብዙ ነገሮች እንደዚያ ይመስሉኛል ተሸፍነን እንጂ ጠንካራ ሰዎች፤አስተማማኝ እና፤ የመላዕክት ህይወት ያላቸው፤ሰዎች የሚንመስለዉ፤ውስጣችን ግን በብዙ ተቦርቡሮ ይሆናል፡፡
    አሁን አሁን በየ አደባባዩ ላይ የሚሰሙት ውድቀቶቻችንም የዚህ ውጤት ይሆናል፡፡እስቲ ሁላችንም ውስጣችንን እንፈትሽ ና ነጻ እንውጣ ፡፡ ውድቀትን ብዙ ሰው ሊያየው ፣ ሊሰማው ይችላል፡፡ ከዚያ በፊት ያለን የውስጥ መቦርቦርና ትናንሽ ልምምዶች ግን እምብዛም አይታይም፡፡ እኛው ከጌታ ጋር አንፍታው፡፡ ልምምዱ ከፍ ያለ ደረጃ እንኩዋ የደረሰ ቢሆን በጾም ጸሎት በፊቱ ብንሆን የማይለወጥ ነገር ምንም የለም፡፡ ጌታ ሁሉን ይችላልና፡፡ ውስጣችን ያለውን፣ የምንቸገርበትን ነገር በሕይወታችን ንጉሥ ለሆነሁ ለአምላከችን እንንጋረዉ፣እርሱ የውስጥን ችግር እንዴት ማሸነፍ እንደሚችል ያዉቃል፡፡
    ንጉሡ ይንገሥ የቀጠላ፡- 1. ክፉ ሐሳብ መላክ፣ 2. ሁኔታዎችን ማመቻቸት..ነው ፡፡ እንጂ የማንንም እጅ ይዞ ና ጠምዝዞ ሐጢያት አያሰራም፡፡ ሔዋንንም ቢሆን በቃልና በሐሳብ ነው የማረካት ድርጊቱን ያደረገችው እርስዋ ነች፡፡ 3. ሐሳብን መበላሸት ነዉ ለሰው ልጆች ሁሉ ውድቀትና ሰበብ የሆነው የሔዋን ስህተት የመጣው ሰይጣን ሐሳቧዋን አበላሽቶት ነው፡፡ 2ቆሮ.11፤3 ፡፡ ሐሳቡ የተበለሸበት ሰው ወደ ድርጊቱ ለመግባት ቀላል ይሆንለታል፤ ልክ እንደ ቃየን ሁሉ የዳዊት ልጅ አቤሴሎምም ወንድሙን አምኖንን ከመግደሉ በፊት ረጅምና የቆየ የግድያ ሐሳብ አርግዞ ነበር፡፡ ጊዜውና ሁኔታዎች ሲመቻቹለት ደግሞ አስገደለው፡፡ (2ሳሙ.13፤23-29) አንዳንድ ጊዜ ክፉ ሐሳብ ያድርና ድርጊቱ ሊቆይ ይችላል፤ ያህን ጊዜ መንቃት ነው፡፡ ምንም እስካላደረኩ ድረስ ንጹህ ነኝ ማለት አይቻልም፡፡ ቀን በሚጠብቅ ክፉ ምኞት ላይ መንገስ ያስፈልጋል፡፤ እግዚአብሔር ቃኤልን ቀድሞ ያስጠነቀቀው ለዚያ ነበረ፡፡ ደጅህ ላይ ሐጢያት እያደባች ነው ንገስባት አለው፡፡ አለዚያ እርሱዋ ትነግስብሃለች፡፡ ያን ጊዜ ፍቃዱዋን ታደርጋለች፡፡ እግዚአብሄር ወደ ቃየን መጥቶ ከነገረው ነገር የምንማረው ኀጢያት ላይ እኛ መንገስ ካልቻልን ኀጢያት በእኛ ላይ መንገስ ይችላል /ይጀምራል/ ማለት ነዉ፡፡ /ዘፍ.4፤7/ “ መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን ?መልካም በታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ፈቃድዋም ወደ አንተ ነዉ÷አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት ” አለዉ፡፡ ያዕቆብ 1፤15 ላይ ሲናገር “ ምኞት ጸንሳ ሐጢያትን ትወልዳለች ፡ሐጢያትም ጸንሳ ሞትን ትወልዳለች ” ሞት የሚባለው /ውድቀት/ነዉ፤ ከመከሰቱ በፊት ውስጥን ይዞ የሚከርመው ሐሳብ /ምኞት/ ነው፡፡ ምኞት ዝም ከተባለ ቆይቶ ቆይቶ ሀጢያትን ይወልዳል፤ ከዚያም ወደ ሞት ያመጣል፤ይህ ሁሉም ሂደት ነው፡፡ ሐጢያትን፣ሞትንና ውድቀትን በህይወቱ ማየት የማይፈልግ ሰው ራሱን ማንጻት ያለበት ከውስጥ ነው፡፡ ምን አርግዣለሁ? ብሎ ራስን መጠየቅ፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታን ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ በቅድሚያ ሐሳብ ነው የመጣለት፡፡ “ ዲያቢሎስም ሐሳብ ካስገባ በሆአላ” አስቆሮቶ ይሁዳ ምናልባት ዲያቢሎስ ወደ አዕምሮው የላከበትን ሐሳብ መቃወም ይችል ነበር ፡፡ ምናልባትም ወደ ሌሎች ደቀመዛሙርትም ዲያቢሎስም ይህንን ሐሳብ አቅርቦም ይሆናል፡፡ ቢሆንም እነርሱ የዲያቢሎስም ሐሳብ ተቃውመውት ይሆናል፡፡ ይሁዳ ግን ሐሳቡን አስተናገደ፤ ወደ ቀጣዩ ና ከባዱ ነገርም አለፈ፡፡ ሮሜ 6፡12 “...ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ '' ስጋችን ላይ ሐጢያት ሲነግስ እንደ ስጋ ፈቃድ ለመኖር የስጋን ነገር አዘውትረን ለማስብ እንገደዳለን” /ሮሜ.8፡5/ ውስጡ የተሸነፈዉን ሰው ወደተገዛለት ነገር በቀላሉ መጎተት ይቻላል፡፡ ብዙ የሚያቅተው ከነገሮች ውስጥ መውጣት ሳይሆን ነገሮችን ከውስጥ ማስወጣት ነው፡፡ እስራኤላውያን በእግራቸው ከግብጽ ውስጥ ወጥተው ነበር፡ ነገር ግን በቆይታ እንደታየው ግብጽ በውስጣቸው ነበረ፡፡ ስለዚህም፡- /ሥራ.7፡39/ “ለእነርሱም አባቶቻችን ሊታዘዙት አልወደዱም፤ነገር ግን በልባቸው ወደ ግብጽ ተመለሱ ይለናል”፡፡ ከዓለም ወጥተን ግን ዓለም በውስጣችን ካለ ፡-እየዘመርን፤እየጸለይን፤ ቤተክርስቲያን እየሄድን፤ የሐጢያት ተጠቂዎች ልንሆን እንችላለን፡፡ከግብጽ ወጥተህ ግብጽ ግን ከልብህ ካልወጣ ችግር ነው፡፡ የሎጥ ሚስት ከሶዶም በእግሩዋ ወጥታለች ነገር ግን ሶዶም ከውስጥዋ አልወጣም ነበርና እንቅፋት ሆነባት፡፡ መቀየር ፣መለወጥ ከውስጥ ነው፡፡ ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል (በሮሜ 12፡3) “ በአዕምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ......" የሚለን፡፡ ከየ ዕለቱ ኑሮአችን እንኩዋ ብንመለከት አንድ ሰው ወተት ወይም ጎመን የሚጠላ ቢሆን፡ ከፈለገ ቦታ ቢመጣም ወይም ነጻም ቢሆን አይነካውም፡፡ ሐጢያትን ከውስጥ ስንጠላ አዩኝ አላዩኝ ከሚል መሳቀቅ እንወጣለን፡፡ በዚህም ላይ ውስጣችንን ቦርቡሮ በጊዜ ሒደት ከሚጥለን ነገር እንገላገላለን፡፡ ልክ እንደ ጎመኑ ና ወተቱ የትም ብንሆን ፣መቼም ቢሆን አንነካውም፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ሲናገር ውስጡ ችግር ያለበት ሰው ያማረ ህንጻ ውስጥ ወይም አውሮፕላን ውስጥ ቢገባ ችግሩ አያቆምም ብሎአል፡፡ የገባበት ቦታ ነገሩን ሊለውጥ ስለማይችል ነዉ፡፡ ከዚህ በፊት አንድ በጣም ወፍራምና ዕድሜ ጠገብ ዝግባ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በሆነ ወቅት ነፋስ ባልነበረበት ጊዜ በሌሊት ላይ ወድቆ ነዉ የተገኘው፤በዘው ጊዜ የወደቀበት ሁኔታው ሲጠና ዛፉ በከፍተኛ ሁኔታ ውስጡ በብል ተቦርቡሮ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ በቅርፊት ተሸፍኖ ያለ እየመሰለ ኖረ እንጂ፤ነገር ግን ባልታሰበ ቀን ቀን ላይ ነዉ ወድቆ የተገኘዉ፡፡ ብዙ ነገሮች እንደዚያ ይመስሉኛል ተሸፍነን እንጂ ጠንካራ ሰዎች፤አስተማማኝ እና፤ የመላዕክት ህይወት ያላቸው፤ሰዎች የሚንመስለዉ፤ውስጣችን ግን በብዙ ተቦርቡሮ ይሆናል፡፡ አሁን አሁን በየ አደባባዩ ላይ የሚሰሙት ውድቀቶቻችንም የዚህ ውጤት ይሆናል፡፡እስቲ ሁላችንም ውስጣችንን እንፈትሽ ና ነጻ እንውጣ ፡፡ ውድቀትን ብዙ ሰው ሊያየው ፣ ሊሰማው ይችላል፡፡ ከዚያ በፊት ያለን የውስጥ መቦርቦርና ትናንሽ ልምምዶች ግን እምብዛም አይታይም፡፡ እኛው ከጌታ ጋር አንፍታው፡፡ ልምምዱ ከፍ ያለ ደረጃ እንኩዋ የደረሰ ቢሆን በጾም ጸሎት በፊቱ ብንሆን የማይለወጥ ነገር ምንም የለም፡፡ ጌታ ሁሉን ይችላልና፡፡ ውስጣችን ያለውን፣ የምንቸገርበትን ነገር በሕይወታችን ንጉሥ ለሆነሁ ለአምላከችን እንንጋረዉ፣እርሱ የውስጥን ችግር እንዴት ማሸነፍ እንደሚችል ያዉቃል፡፡
    0 Yorumlar 0 hisse senetleri 56 Views 0 önizleme
  • አርብ ጥቅምት 7/2018 አ/ም በነበረን ፕሮግራም ድንቅ የአምልኮ፣የቃል የፈውስ እና የፀሎት ጊዜን ጌታ ሰጥቶናል።በሁሉ የረዳን ጌታ ይመስገን።
    አርብ ጥቅምት 7/2018 አ/ም በነበረን ፕሮግራም ድንቅ የአምልኮ፣የቃል የፈውስ እና የፀሎት ጊዜን ጌታ ሰጥቶናል።በሁሉ የረዳን ጌታ ይመስገን።
    0 Yorumlar 0 hisse senetleri 52 Views 0 önizleme
  • የእግዚአብሔር ድንቅ ፈቃዱ ቢሆን ጥቅምት 7 አርብ ምሽት ከ11.30 ጀምሮ የፈውስ እና የነፃ የመውጣት ጊዜ ይኖራል!! እንድሁም ጥቅምት 9 እሁድ ጠዋት ከ2.30 እስከ 3.30 የትምህርትና የጸሎት ጊዜ ስሆን ከሦስት ሰዓት ተኩል እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ ድንቅ የሆነ የአምልኮ፤የቃል የመፈታት እና የአርነት ጊዜ ይሆናል፦ ቅዱሳን በሙሉ ከእኛ ጋር ጌታን ለመገልገል ወደ አለም ባንክ አጥቢያ ይምጡ እና ይገልገሉ ያገለግሉ!!
    የእግዚአብሔር ድንቅ ፈቃዱ ቢሆን ጥቅምት 7 አርብ ምሽት ከ11.30 ጀምሮ የፈውስ እና የነፃ የመውጣት ጊዜ ይኖራል!! እንድሁም ጥቅምት 9 እሁድ ጠዋት ከ2.30 እስከ 3.30 የትምህርትና የጸሎት ጊዜ ስሆን ከሦስት ሰዓት ተኩል እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ ድንቅ የሆነ የአምልኮ፤የቃል የመፈታት እና የአርነት ጊዜ ይሆናል፦ ቅዱሳን በሙሉ ከእኛ ጋር ጌታን ለመገልገል ወደ አለም ባንክ አጥቢያ ይምጡ እና ይገልገሉ ያገለግሉ!!
    0 Yorumlar 0 hisse senetleri 52 Views 0 önizleme
  • ፡ንጉሡ ይንገሥ የቀጠላ :-
    (ዮሐ1፡50) “ናትናኤልም መልሶ፡-መምር ሆይ÷አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለዉ”
    ንጉሡ ለምን ይንገሥ?
    1. እንደ ብርሃን ልጆች በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ብለን እንድንታይ፡፡
    (ዮሐ 8፡12 ማቴ 5፡14-16)
    2. መጣል ያለበትን መጥፎ ነገሮችን ከእኛ ሕይወት ጥሎልን ክብሩን ልገልጥ፡፡
    (ሐ/ሥ 9፡5- ማር 10፡49-50)
    3. ከዉስጣችን መወገድ ያለዉን ክፉ ዘር አስወግዶ ፍሬያማዎች ልያደርገን፡፡
    (ማር 7፡20-23 ገለትያ 5፡19-25)
    4. ያደከማዉን ድካም ከዉስጣችን አዉጥቶ በብርታት እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለማስታጠቅ ፡፡ (ሐ/ሥ 2፡36-41 ማሳ 6፡14-18 )
     የእግዚአብሄር ጥያቄ
    እግዚአብሄር በዘመናት ሁሉ መካከል ለአገር፣ ለቤ/ክርስቲያን፣ ለግለሰብና ለትውልድ ጥያቄ አለው። የእግዚአብሄር ጥያቄዎች ከእኛ መልስ ይሻሉ፤ እግዚአብሄር መልስ የሌለውና የማናውቀውን ጥያቄ አይጠይቀንም።
    አንዳንዴ በገሀዱ አለም እንደምናየውም፣ እንደምንሰማውም አጥርቶ ካለመስማት ከጥያቄው ጋር ፈፅሞ አብሮ የማይሄድ መልስ እንመልሳለን፤ ወይም በግምት የመሰለንን እንመልሳለን፤ አንዳንዴም በህብረተሰባችን ዘንድ እንደ አዋቂ ከተቆጠርን አያውቅም ላለመባልና አላውቅም ላለማለት ነገሮችን እናወሳስባቸዋለን።
    ለጥያቄው የጥያቄ መልስ እንሰጣለን፤ ወይም ከሌሎች የምንሻልበትን (የተሻልንበትን) በዚያ ራሳችንን እንመለከታለን። እግዚአብሄር ግን የጠቅላላ እውቀት ጥያቄ ሳይሆን የግል ጥያቄዎች ለእያንዳንዳችን የሚጣይቃዉ። አዎን እግዚአብሄር ዛሬም ጥያቄ አለው።
    በተለይ የመንፈሳዊነት ጭምብል በበዛበት በአሁኑ ዘመን እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን ጥያቄ አለው። ከዚህ በታች ለሚቀጥሉት እግዚአብሄራዊ ለሆኑ ጥያቄዎች እውነተኛ የሆነ መልስ እንስጥ ማንም በማይሰማበት በግል ስፍራችን መልሱን ለጌታ እንመልስ፣ ከእርሱ ጋር እንስማማ፣ ጥያቄው ካልገባን ደግሞ ጌታ ሆይ አልገባኝም ብሎ በትህትና መጠየቅ ብልህነት ነው።
    ብልጣብልጥነት ለያዕቆብም አልበጀውም! እግዚአብሄር ዘልቆ ያያል፤ እግዚአብሄር አይታለልም፣ በፊታችን ላለው ረጅም ጉዞ አብሮ ለመጓዝ ለእግዚአብሄር ጥያቄዎች መልስ እንስጥ።
    ንጉሡ እንዲነግሥ ከእኛ ምን ይጠበቃል? ይቀጥላል፡-
    ፡ንጉሡ ይንገሥ የቀጠላ :- (ዮሐ1፡50) “ናትናኤልም መልሶ፡-መምር ሆይ÷አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለዉ” ንጉሡ ለምን ይንገሥ? 1. እንደ ብርሃን ልጆች በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ብለን እንድንታይ፡፡ (ዮሐ 8፡12 ማቴ 5፡14-16) 2. መጣል ያለበትን መጥፎ ነገሮችን ከእኛ ሕይወት ጥሎልን ክብሩን ልገልጥ፡፡ (ሐ/ሥ 9፡5- ማር 10፡49-50) 3. ከዉስጣችን መወገድ ያለዉን ክፉ ዘር አስወግዶ ፍሬያማዎች ልያደርገን፡፡ (ማር 7፡20-23 ገለትያ 5፡19-25) 4. ያደከማዉን ድካም ከዉስጣችን አዉጥቶ በብርታት እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለማስታጠቅ ፡፡ (ሐ/ሥ 2፡36-41 ማሳ 6፡14-18 )  የእግዚአብሄር ጥያቄ እግዚአብሄር በዘመናት ሁሉ መካከል ለአገር፣ ለቤ/ክርስቲያን፣ ለግለሰብና ለትውልድ ጥያቄ አለው። የእግዚአብሄር ጥያቄዎች ከእኛ መልስ ይሻሉ፤ እግዚአብሄር መልስ የሌለውና የማናውቀውን ጥያቄ አይጠይቀንም። አንዳንዴ በገሀዱ አለም እንደምናየውም፣ እንደምንሰማውም አጥርቶ ካለመስማት ከጥያቄው ጋር ፈፅሞ አብሮ የማይሄድ መልስ እንመልሳለን፤ ወይም በግምት የመሰለንን እንመልሳለን፤ አንዳንዴም በህብረተሰባችን ዘንድ እንደ አዋቂ ከተቆጠርን አያውቅም ላለመባልና አላውቅም ላለማለት ነገሮችን እናወሳስባቸዋለን። ለጥያቄው የጥያቄ መልስ እንሰጣለን፤ ወይም ከሌሎች የምንሻልበትን (የተሻልንበትን) በዚያ ራሳችንን እንመለከታለን። እግዚአብሄር ግን የጠቅላላ እውቀት ጥያቄ ሳይሆን የግል ጥያቄዎች ለእያንዳንዳችን የሚጣይቃዉ። አዎን እግዚአብሄር ዛሬም ጥያቄ አለው። በተለይ የመንፈሳዊነት ጭምብል በበዛበት በአሁኑ ዘመን እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን ጥያቄ አለው። ከዚህ በታች ለሚቀጥሉት እግዚአብሄራዊ ለሆኑ ጥያቄዎች እውነተኛ የሆነ መልስ እንስጥ ማንም በማይሰማበት በግል ስፍራችን መልሱን ለጌታ እንመልስ፣ ከእርሱ ጋር እንስማማ፣ ጥያቄው ካልገባን ደግሞ ጌታ ሆይ አልገባኝም ብሎ በትህትና መጠየቅ ብልህነት ነው። ብልጣብልጥነት ለያዕቆብም አልበጀውም! እግዚአብሄር ዘልቆ ያያል፤ እግዚአብሄር አይታለልም፣ በፊታችን ላለው ረጅም ጉዞ አብሮ ለመጓዝ ለእግዚአብሄር ጥያቄዎች መልስ እንስጥ። ንጉሡ እንዲነግሥ ከእኛ ምን ይጠበቃል? ይቀጥላል፡-
    0 Yorumlar 0 hisse senetleri 52 Views 0 önizleme
EAG AB Church https://eagalembankchurch.com