Gospel singer: Azeb Hailu

የጌታ  ስራ



የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል
የጌታ ፡ ሥራ ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል
ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ
በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ

ነግሮ ፡ ሊጨርስ ፡ ማነው ፡ የቻለ
ተዓምራቶቹን ፡ እያስተዋለ
የጌታን ፡ ክብር ፡ ታላቅነቱን
የፍቅሩን ፡ ብዛት ፡ ደግሞ ፡ ጥልቀቱን

ከመታወቅም ፡ ሁሉ ፡ ያለፈ
ከህሊናችን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈ
ነውና ፡ ታላቅ ፡ ሥራው ፡ ብዙ
ለዚህ ፡ ለጌታ ፡ ምሥጋናውን ፡ አብዙ

ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ፍጥረት ፡ የሚያመሰግንህ
ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ክብር ፡ ለአንተ ፡ የተገባ
ስለሆንክ ፡ ገዢ ፡ ብርቱና ፡ ገናና
አሁንም ፡ አሁንም ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና

ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ በግዛትህ ፡ ናቸው
ስለዚህም ፡ በአንተ ፡ ብዙ ፡ ደስታ ፡ አላቸው
በራሳቸው ፡ ቋንቋ ፡ ይመሰክራሉ
የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ ፍጥረት ፡ ነን ፡ እያሉ ፡ ሃሌሉያ

የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ
የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ

እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ ይህን ፡ ይመስላል
ተብሎ ፡ በቃላት ፡ መች ፡ ይገለጻል
አንዲያ ፡ ልጁ ፡ በቀኙ ፡ ያለው
ተረከው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አየው

ዛሬ በሰራው ስታሞግሱ
ደግሞ ማለዳ አዲስ ነው እሱ
መልካምነቱ ከቶ አያልቅበት
አደራረጉን አቤት ሲያውቅበት

በደማቅ ፡ ብርሃን ፡ እራስክን ፡ ሰውረህ
ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ብለህ
ድካምና ፡ ዝለት ፡ ሳያውቅህ ፡ እርጅና
ትናንትና ፡ ዛሬም ፡ ሁልጊዜ ፡ ገናና

ንጉሥ ፡ በንግሥናው ፡ አዋቂው ፡ በዕውቀቱ
ሊመስልህ ፡ ሲሞክር ፡ ሲጥር ፡ አይ ፡ ሰው ፡ ከንቱ
ነገር ፡ ግን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሁሉን ፡ ሲያስተያይ
ሁሉን ፡ ብሎ ፡ ያልፋል ፡ የለህም ፡ መሳይ ፡ ሃሌሉያ

የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ
የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ

እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ ይህን ፡ ይመስላል
ተብሎ ፡ በቃላት ፡ መች ፡ ይገለጻል
አንዲያ ፡ ልጁ ፡ በቀኙ ፡ ያለው
ተረከው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አየው

ሰማይ ፡ ተቀምጦ ፡ እግሮቹ ፡ ምድር
ታላቅነቱ ፡ እንዴት ፡ ይነገር
መግለጫ ፡ ቋንቋ ፡ ቢጠፋም ፡ ቃሉ
እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ተመሥገን ፡ በሉ

የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል
የጌታ ፡ ዝና ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል
ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ
በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ

ዛሬ በሰራው ስታሞግሱ
ደግሞ ማለዳ አዲስ ነው እሱ
መልካምነቱ ከቶ አያልቅበት
አደራረጉን አቤት ሲያውቅበት

በምስጋና ላይ ደግሞ ምስጋና
በአፋችሁ ላይ ይጨምርና
በልቦናቸው መደነቅ ሞልቶ
ሳይነዋወጥ ይኖራል ፀንቶ


የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ
የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
Gospel singer: Azeb Hailu የጌታ  ስራ 🎼🥁🎸🎷🎹🪘🎻🎤 የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል የጌታ ፡ ሥራ ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ነግሮ ፡ ሊጨርስ ፡ ማነው ፡ የቻለ ተዓምራቶቹን ፡ እያስተዋለ የጌታን ፡ ክብር ፡ ታላቅነቱን የፍቅሩን ፡ ብዛት ፡ ደግሞ ፡ ጥልቀቱን ከመታወቅም ፡ ሁሉ ፡ ያለፈ ከህሊናችን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈ ነውና ፡ ታላቅ ፡ ሥራው ፡ ብዙ ለዚህ ፡ ለጌታ ፡ ምሥጋናውን ፡ አብዙ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ፍጥረት ፡ የሚያመሰግንህ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ክብር ፡ ለአንተ ፡ የተገባ ስለሆንክ ፡ ገዢ ፡ ብርቱና ፡ ገናና አሁንም ፡ አሁንም ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ በግዛትህ ፡ ናቸው ስለዚህም ፡ በአንተ ፡ ብዙ ፡ ደስታ ፡ አላቸው በራሳቸው ፡ ቋንቋ ፡ ይመሰክራሉ የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ ፍጥረት ፡ ነን ፡ እያሉ ፡ ሃሌሉያ የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ ይህን ፡ ይመስላል ተብሎ ፡ በቃላት ፡ መች ፡ ይገለጻል አንዲያ ፡ ልጁ ፡ በቀኙ ፡ ያለው ተረከው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አየው ዛሬ በሰራው ስታሞግሱ ደግሞ ማለዳ አዲስ ነው እሱ መልካምነቱ ከቶ አያልቅበት አደራረጉን አቤት ሲያውቅበት በደማቅ ፡ ብርሃን ፡ እራስክን ፡ ሰውረህ ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ድካምና ፡ ዝለት ፡ ሳያውቅህ ፡ እርጅና ትናንትና ፡ ዛሬም ፡ ሁልጊዜ ፡ ገናና ንጉሥ ፡ በንግሥናው ፡ አዋቂው ፡ በዕውቀቱ ሊመስልህ ፡ ሲሞክር ፡ ሲጥር ፡ አይ ፡ ሰው ፡ ከንቱ ነገር ፡ ግን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሁሉን ፡ ሲያስተያይ ሁሉን ፡ ብሎ ፡ ያልፋል ፡ የለህም ፡ መሳይ ፡ ሃሌሉያ የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ ይህን ፡ ይመስላል ተብሎ ፡ በቃላት ፡ መች ፡ ይገለጻል አንዲያ ፡ ልጁ ፡ በቀኙ ፡ ያለው ተረከው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አየው ሰማይ ፡ ተቀምጦ ፡ እግሮቹ ፡ ምድር ታላቅነቱ ፡ እንዴት ፡ ይነገር መግለጫ ፡ ቋንቋ ፡ ቢጠፋም ፡ ቃሉ እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ተመሥገን ፡ በሉ የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል የጌታ ፡ ዝና ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ዛሬ በሰራው ስታሞግሱ ደግሞ ማለዳ አዲስ ነው እሱ መልካምነቱ ከቶ አያልቅበት አደራረጉን አቤት ሲያውቅበት በምስጋና ላይ ደግሞ ምስጋና በአፋችሁ ላይ ይጨምርና በልቦናቸው መደነቅ ሞልቶ ሳይነዋወጥ ይኖራል ፀንቶ የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
0 Yorumlar 0 hisse senetleri 56 Views 0 önizleme
Eag Alembank https://eagalembankchurch.com