ስለ #መጽሐፍ_ቅዱስ ምን ያህል ያውቃሉ...?

❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
• 66 መጽሐፍት
• 1,189 ምዕራፎች
• 31,173 አንቀፆች
• 810,697 ቃላት
• 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ።

❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን
• በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ
• በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119
• አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው።

❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው።

❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው።

❖ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል።

❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው።
ይኸውም፦
• መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት።

• የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው።

• የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21)

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ
"ድመት" ብቻ ናት።
ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ
እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ
ስለ ፀሎት 400 ጊዜ
ስለ እምነት 500 ጊዜ
ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።
📖ስለ #መጽሐፍ_ቅዱስ ምን ያህል ያውቃሉ...? ❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው። ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ • 66 መጽሐፍት • 1,189 ምዕራፎች • 31,173 አንቀፆች • 810,697 ቃላት • 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ። ❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን • በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ • በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119 • አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው። ❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው። ❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው። ❖ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል። ❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው። ይኸውም፦ • መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት። • የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው። • የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው። ❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል። ❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21) ❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል። ❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ "ድመት" ብቻ ናት። ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል። ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው። ❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስለ ፀሎት 400 ጊዜ ስለ እምነት 500 ጊዜ ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል። ❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።
0 التعليقات 0 المشاركات 2كيلو بايت مشاهدة 0 معاينة