https://t.me/KALTUBE/11424
https://t.me/KALTUBE/11424
T.ME
#KALTUBE
ከሰፈር ውጪ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ከሰጣቸው የአምልኮ ስርዓት ውስጥ አንዱ ንጹሕ ያልሆነ ወይም የረከሰን ነገር ከሰፈራቸው ውጪ እንዲያስወጡ የሚያዝ ነበር:: በተለያዩ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች እስኪሻላቸው ድረስ ከሰፈር ውጪ እንዲቆዩ ይደረግ ነበር:: ይህ ብቻ ሳይሆን በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በሚደረገው የስርየት ቀን ላይ ሊቀ-ካህኑ ሁለት ፍየሎችን በማዘጋጀት የህዝቡን ሁሉ ኅጢአት ይናዘዝባቸዋል:: አንደኛውን በማረድ ደሙን ያፈሰዋል:: ሁሉተኛውን ደግሞ ወደ ምድረበዳ እንዲወሰድ ያደርገዋል:: ይህም እግዚአብሔር ኅጢአታችንን ከእኛ አርቆታል የሚለውን ለማመልከት ነው:: ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር ኅጢአታችንን በሙሉ በልጁ በኢየሱስ ላይ አኖረው:: እርሱም የግርፋት እና የስቅላት ፍርድ በተፈረደበት ዕለት: ህዝቡ ሁሉ እና ወታደሮቹ ከጲላጦስ ፊት አውጥተው የራስ ቅል ወደሚባለው ቀራኒዮ ጎልጎታ ከሰፈራቸው ውጪ ወሰዱት:: ዘላለማዊው ንጹህ እና ቅዱስ ጌታ እንደ ቆሻሻ እና ርኩስ ተቆጠረ:: የተረገመ ሰው በሚሰቀልበት እንጨት ላይ ሰቀሉት:: ይህንን ሁሉ ያደረገው ኅጢአታችንን ሊወስድልን እና የእርሱን ጽድቅ ሊሰጠን ነው:: ወደ ዕብራውያን 13:11-14 መከራን ወደተቀበለው፣ወደሚያድነው እና የዘላለም ህይወት ወደሚሰጠው ወደ ኢየሱስ ልትመጣ ትወዳለህ? ልንረዳህ በዚህ አለን። #ያ_መሲሕ #እነሆ_ያመሲሕ #ኑ_ወደ_ኢየሱስ #ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ Follow Meskerem Getu on: Facebook | Instagram | TikTok | Threads Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest
0 التعليقات 0 المشاركات 250 مشاهدة 0 معاينة